Mols.gov.et

”የግብርና ኮሌጆቻችንን ትራንስፎርም የማድረግ ጉዳይ የአመራሩን ባለቤትነት ይፈልጋል” ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

August 30, 2023
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የግብርና ኮሌጆች የትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ እንደገለፁት፤ የግብርና ኮሌጆችን ትራንስፎርም ማድረግ በክህሎት ልማት ዘርፉ ከያዝነው የሪፎርም ሀሳብ አንፃር ትልቁና ዋነኛው ነው፡፡ ይህም የአመራሩን ባለቤትነት ይፈልጋል። ከዚህ አንፃር ኮሌጆቹ ባላቸው የልማት ፀጋ የጀመሩት ሥራ መልካም ቢሆንም ካላቸው ሀብት፣ የመልማት ፀጋ እና መድረስ ከምንፈልግበት ግብ አኳያ ሲመዘን የተጀመረው ሥራ በቂ አይደለም፡፡ ዛሬ የሚደረገው ውይይትም በመስክ ምልከታ ቡድኑ የቀረቡ ግንኝቶችን የጋራ ከማድረግ ባሻገር ትራንስፎርሜሽኑን ለማሳካት የመፍትሄ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን ላይ የጋራ ግንዛቤ የምንይዝበተ ነው ብለዋል፡፡ ሥራዎችን በፍጥነትና በግዜ የለንም መንፈስ መስራት እንደሚገባ የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ካሉብን ችግሮች በላይ በመሆን የታሰበውን ግብ ለማሳካት መረባረብ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top