Mols.gov.et

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን አስመልክተዉ ከተናገሩት፡-

November 22, 2022
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን አስመልክተዉ ከተናገሩት፡- የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተመሰረተ አንድ ዓመት ቢሆንም እጅግ አመርቂ ስራ ከሚሰሩ ተቋማት አንዱ ነዉ፡፡ በአንድ ዓመት ጊዜ ዉስጥ 10 ዓመት እንደቆየ ተቋም እራሱን አደራጅቶ ለረዥም ጊዜ የሁላችንም ጥያቄ የነበረዉ የስራ መረጃ በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ የመስራት ስራ ጀምረናል፡፡ ይህ ደግሞ በየአካባቢዉ በየእለቱ እየተፈጠረ ያለ ስራ ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ያስችለናል፡፡ በዚህ ቴክኖሎጂ ታግዘን እንደ አደጉት ሀገራት በየእለቱ ስንት ሰዉ ስራ እንዳገኘ፣ ስራ እንደቀየረ እና እንደተመዘገበ ትክክለኛ መረጃ መግኘት እንችላለን፡፡ ኢትዮጵያ ዉስጥ ስራ የሰዉ ያለህ ብሎ ይጮሃል ሰራተኛዉ ደግሞ የሥራ ያለህ ብሎ ይጮሃል ጠፍቶ የነበረዉ ድልድይ ሆኖ የሚያገናኝ አካል ነበር፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተቋቋመዉ ሥራዉ እና ሰሪዉን ድልድይ ሆነዉ እንዲያገናኝ ነዉ፡፡
en_USEN
Scroll to Top