Mols.gov.et

የጀነራል ውንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የዓለም አቀፍ …

February 29, 2024
የጀነራል ውንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የዓለም አቀፍ የጥራት ሥራ ዓመራር ሰርተፊኬት ባለቤት ሆነ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የጀነራል ውንጌት ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ቀዳሚ በመሆን የጥራት ሥራ አመራር(ISO 900,2015) ሰርተፊኬት ዛሬ ተረክቧል፡፡ በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ነቢሃ መሀመድ፤ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት የሥልጠና ጥራት ለማረጋገጥ የጥራት ሥራ አመራር(ISO 900,2015) ተግባራዊ ማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽዎ እንዳለው ገልጸው ፋይዳውን ቀድሞ በመረዳት እና አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች አጠናቆ የጥራት ሥራ አመራር ሰርተፊኬት በመረከብ ጀነራል ውንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቀዳሚ ሆኗል ብለዋል፡፡ በቀጣይም ልከ እንደ ጀነራል ውንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተለያዩ ኮሌጆች ወደ ጥራት ሥራ አመራር(ISO 900,2015) ለመግባት ሰፊ ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኝ ጠቁመው በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ሰልጣኞች በሀገር ውስጥም ይሁን በተቀረው ዓለም ተወዳዳሪ እና ተፈላጊ እንዲሆኑ ዓለም አቀፍ የሥራ አመራር ጥራት ተግባራዊ ማድረግ አማራጭ የሌለው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ የጥራት ሥራ አመራር ሰርተፍኬቱን ለኮሌጁ ያስረከቡት የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራ፣ የጥራት ሥራ አመራር(ISO 900,2015) ወጥ የሆነ የትምህርት ጥራት ተግባራዊ ለማድረግና ብክነትን ለመቀነስ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡ የኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው በበኩላቸው የጥራት ሥራ አመራር(ISO 900,2015) ሰርተፍኬት ባለቤት መሆናችን በቀጣይ የምስራቅ አፍሪካ የኢነርጂ ዘርፍ የልህቀት ማዕከል ለመሆን የምናደርገውን ጥረት በእጅጉ ያግዛል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ ተቋሙ የጥራት ሥራ አመራር ሰርተፍኬት ባለቤት እንዲሆን ጉልህ አስተዋጽዎ ያበረከቱ አካላት እውቅናና ምስጋና ተችሯቸዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top