Mols.gov.et

የጀርመን የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር…

January 30, 2024
የጀርመን የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር የመካከለኛው፣ምስራቅና የደቡብ አፍሪካ አገራት ዳይሬክተር ፊሊፕ ኒል ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡ በውይይታችን በጀርመን እና ኢትዮጵያ መካከል በትምህርትና ሥልጠና፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በድህነት ቅነሳ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ እየተተገበሩ ያሉ የልማት እና የትብብር ሥራዎችን በዝርዝር ተመልክተናል፡፡ በዚህም በሀገሪቱ የልማትና ትብብር ሥራ ውስጥ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ የሚገኘው የጀርመን የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን የገንዘብ እና የቴክኒክ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠውልናል፡፡ የጀርመን የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ፊሊፕ ኒል ላደረጉልን ደማቅ አቀባበል እና የሁለቱን ሀገራት የረዥም ጊዜ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ላሳዩት ቀርጠኛ አመራር ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ!
en_USEN
Scroll to Top