Mols.gov.et

የድጋፍና ክትትል ሥራው ለሚገጥሙ ችግሮች በወቅቱ መፍትሄ በመስጠት የዘርፉን አፈፃፁም ለማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው። የኦሮሚያ ክልል

November 22, 2024
የድጋፍና ክትትል ሥራው ለሚገጥሙ ችግሮች በወቅቱ መፍትሄ በመስጠት የዘርፉን አፈፃፁም ለማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው። የኦሮሚያ ክልል በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ ሙሃመድ የተመራው የድጋፍና ክትትል ቡድን በኦሮሚያ ክልል የመስክ ምልከታ እያደረገ ነው። የድጋፍና ክትትል ቡድኑ ከክልሉ የሥራ ሀላፊዎች ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ ከክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት አኳያ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተከናወኑ ሥራዎች፣ የተገኙ ውጤቶችንና የነበሩ ውስንነቶችን በዝርዝር ተመልክቷል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ ሙሃመድ፣ የድጋፍና ክትትል ሥራው ዋና ዓላማ በአፈፃፀም የታዩ ማነቆዎችን በጋራ በመለየትና በመፍታት ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የዘርፉ አፈፃፀም ቀጣይነት ባለው መልኩ ማሻሻል ነው። ቡድኑ ከአመራሩ ጋር ከሚያደረገው ውይይት ባሻገር በተመረጡ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች፣ በኢንተርፕራይዞች እና በኢንዱስትሪዎች የመስክ ምልከታ ያደርጋል ብለዋል። ለክልል፣ ለዞንና ወረዳ አመራሮች በአዲሱ የዘርፉ እሳቤዎችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ቡድኑተሰጥቷል። በመድረኩ ላይ የተገኙ የክልሉ የዘርፉ አመራሮች በበኩላቸው የድጋፍና ክትትል ሥራው ለሚገጥሙ ችግሮች በወቅቱ መፍትሄ በመስጠት የዘርፉን አፈፃፁም ለማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው። ስለሆነም የድጋፍና ክትትል ሥራው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።
en_USEN
Scroll to Top