Mols.gov.et

የድጅታል መሰረተ ልማት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት

October 20, 2023
የድጅታል መሰረተ ልማት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደውና ሥራ ፈላጊ ምሩቃን ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር በአንድ ባገናኘው የሥራ አውደ ርዕይ የተለያዩ የፓናል ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡ የኢተዮጵያ ትምህርት ስርዓት ወደ ድጅታል ማሸጋገር እና ለመጪው ትውልድ ያለው ጠቀሜታ ላይ ባተኮረው የፓናል ውይይት ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በፓናሊስትነት ተሳትፈዋል፡፡ ሚኒስትር ደኤታው ባቀረቡት ማብራሪያ እንደገለጹት ቀደም ባሉት ዓመታት የድጅታል ክህሎት በትምህርት ተቋማት ትኩረት ተነፍጎት እንደቆየ ጠቅሰው በአሁን ወቅት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የድጅታል መሰረተ ልማት ለማስፋፋት ሰፊ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም ተማሪዎች በትምህርት ተቋማት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ክህሎት ይዘው እንዲወጡ ለማስቻል በአሁን ወቅት በተለይ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት 160 የሚሆኑ የትምህርት ካሪኩለሞች ላይ ክለሳ ተደርጓል ብለዋል፡፡
Scroll to Top