Mols.gov.et

“የደህንነት ተቋማት የሀገራችን ዋስትና በመሆናቸው የተደራጁበትን ዘመናዊ ተክለቁመና በመመልከታችን ተደስተናል።”

July 22, 2022
“የደህንነት ተቋማት የሀገራችን ዋስትና በመሆናቸው የተደራጁበትን ዘመናዊ ተክለቁመና በመመልከታችን ተደስተናል።” ክቡር በከር ሻሌ(ዶ/ር) የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና በአሠሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፎች ከደህንነት ተቋማት ጋር መስራትን መሰረት ያደረገ ጉብኝት አካሂዷል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት ዋናውን መስሪያ ቤት በጎበኙበት ወቅት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር በከር ሻሌ(ዶ/ር) እንደተናገሩት የመከላከያ ዋናው መስሪያ ቤት ከኢትዮጵያውያን አልፎ አፍሪካውያንን የሚሰበስብ የሁሉም ቤት ነው። ከመከላከያ ሚኒስቴር ጋር በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በክህሎት ልማት እና በሥራ ቦታ ደህንነት በለየናቸው መስኮች ጠንካራ ሥራዎችን በጋራ መስራት ጀምረናል ያሉት ክቡር በከር ሻሌ(ዶ/ር) የደህንነት ተቋማት የሀገራችን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ዋስትና በመሆናቸው የተደራጁበትን ዘመናዊ ተክለ ቁመና በመመልከታችን ተደስተናል ብለዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሠራተኞችም ዘመኑ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ በታጠቀው እና የኢትዮጵያን ልክ በሚያሳይ መልኩ በተደራጀው መከላከያ ሠራዊት ዋና መስሪያ ቤት ኩራት እንደተሰማቸው ገልፀዋል።
en_USEN
Scroll to Top