Mols.gov.et

የዜጎች ክብርና ደህንነት ተጠብቆ በውጭ ሀገራት …

February 21, 2024
የዜጎች ክብርና ደህንነት ተጠብቆ በውጭ ሀገራት ምቹ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የመዳረሻ ሀገራትን የማስፋት ጥረታችንን አጠናክረን ቀጥለናል:: ዛሬ ዶሀ ተገኝተን ከኳታር የሌበር ሚንስትር ክቡር ዶ/ር ዓሊ ቢን ሳሚክ አል ማሪ ጋር ጠቃሚ ውይይት አድርገናል:: ይህ የሌበር ዲፕሎማሲ የሥራ ዕድልን ከማስፋት ባሻገር ሀገራችን ከኳታር ጋር ያላትን የረጅም ግዜ የእህትማማችነት ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችል ነው:: ቀደም ሲል ከነበረው የቤት ውስጥ ሥራ ስምሪት ባሻገር በአዲስ መልክ የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ (Skilled and Semi-skilled) የሰው ኃይል ለኳታር የሥራ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ላይ ደርሰናል:: ለነበረን ፍሬያማ ውይይት ክቡር ሚንስትር ዶ/ር ዓሊ ቢን ሳሚክ አል ማሪን ከልብ አመሰግናለሁ!
en_USEN
Scroll to Top