በሀገሪቱ ከሚገኙ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ አስተባባሪዎች እና የገጠር የሥራ ዕድል ፈጠራ ዳይሬክተሮች የሚሳተፉበት ስልጠና በሰንዳፋ ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ መስጠት ተጀምሯል፡፡
ሥልጠናውን ያስጀመሩት ክብርት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የዘርፉ ተልዕኮ መሳካት የኢኮኖሚ ነጻነታችንን በማረጋገጥ የድህነት ታሪካችንን በመቅበር አዲስ የዕድገትና ብልጽግና ታሪክ እውን ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
አክለውም መድረኩ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ እንዲሆን የተደረገው እጅግ ውድ የሆነውን ህይወታቸው ለሀዝብ በነጻ ከሚሰጡ ፖሊሶች የሕይወት ተሞክሮ በትንሹም ቢሆን ልምድ ለመውሰድ በማሰብ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በስልጠናው ቆይታ የዘርፉ አዳዲስ እሳቤዎች ስርጸት እና አፈጻጸም እንዲሁም በቀጣይ የሚተገበሩ ሥራዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር መስፍን አበበ በበኩላችሁ የህዝብ ጥቀምን ማስቀደም ከፖሊስ ትምህርት በመውሰድ ህዝብንና ሀገርን ወደፊት የሚያሻግሩ ተግባራት ማከናወን ይገባል ብለዋል፡፡