Mols.gov.et

የዘርፉን አዲስ እሳቤ …

April 26, 2024
“የዘርፉን አዲስ እሳቤ በተገቢው መልኩ ለመተግበር የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል።” ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ መሃመድ የሥራና ክህሎት አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት ከአዲስ አበባ መስተዳድር የሥራና ክህሎት፣ የሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ ዲኖች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ መሃመድ የሚኒስቴር መ/ቤቱ የሰፐር ቪዥን ቡድን አባላት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዘርፉ ሥራዎችን ላይ ቅኝት ሲያካሄድ መቆየታቸውን ገልፃዋል፡፡ ባለፉት 20 ቀናት በተካሄደው የመስክ ምልከታ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን ከአዲሱ የዘርፉ እሳቤ መሠረት ከመቃኘት አንፃር ተስፋ ሰጪ ጅምሮች መስተዋላቸውን የገለፁት ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ በዘርፎች መካከል ቅንጅትን ከመፍጠርና የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ላይ ተሳታፊ ለሚሆኑ ዜጎች ተገቢውን ሥልጠና እና ምዘና ከመስጠት አንፃር ግን ክፍተት መስተዋሉን አስታውቀዋል፡፡ ክፍተቶቹን መነሻ በማድረገም በመድረኩ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍን አዲስ እሳቤ፣ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓትን እና የውጭ አገር ሥራ ስምሪትን የተመለከቱ ገለፃዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እየተገበረ የሚገኘውን የዘርፉን አዲስ እሳቤ መነሻ በማድረግ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጥራትንና ውጤታማነትን ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ መሀመድ በመጠቆም ለሥራ ወደ ውጭ አገራት የሚሰማሩ ወገኖች ተገቢውን ሥልጠና አግኝተው፣ ተመዝነው እንዲሁም ህጋዊ መንገድን ተከትለው እንዲሄዱ ለማስቻል የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top