Mols.gov.et

የዓለም-አቀፍ ስታርትአፕ ሽልማት የአፍሪካ ጉባኤን (Global StartUp Award Summit 2023) ዛሬ በይፋ አስጀምረናል፡፡

October 25, 2023
የዓለም-አቀፍ ስታርትአፕ ሽልማት የአፍሪካ ጉባኤን (Global StartUp Award Summit 2023) ዛሬ በይፋ አስጀምረናል፡፡ ጉባኤው በአፍሪካ ለስታርትአፕ ምቹ የሆነ ስነ-ምህዳር መፍጠር እና ስኬታማ የሆኑ የአፍሪካ ስታርትአፖች፣ ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሁም የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ተገቢውን የክህሎት፣ የእውቀት፣ የቴክኖሎጂና የገንዘብ ድገፍ የሚያገኙበትን ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስችል፣ አፍሪካውያን የፈጠራ ወጣቶችን ወደ ዓለም አቀፉ ስነ-ምህዳር የሚያስገባ እና ትላንት ያስጀመርነውን የቀጣይ የኢትዮጵያ የስታርት አፕ ማዕቀፍን (Next Ethiopian Startup – NEST) የሚያጠናክር ነው፡፡ ጉባኤው እንደ ሀገር የተለምነውን የኢትዮጲያን ብልጽግና የማሳካት ራዕይ ታሳቢ በማድረግ ፈጠራን መሰረት ያደረገ ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችሉና ተሞክሮና ልምድ የሚወሰድባቸው አጀንዳዎችና ጥናቶች የሚቀርቡበት እንዲሁም የፈጠራና ቴክኖሎጂ ስነ-ምህዳሩን ለመገንባት የሚያስችሉ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩበት ትልቅ መድረክ ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያ ኢኖቬሽን፣ ቴክኖሎጂ እና ሥራ ፈጠራን ለማስፋፋት ላሳዩት ቁርጠኝነትና ለሰጡት አመራር ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ፡፡ ስራው የተሳካ እንዲሆን አበርክቶ የነበራችሁ ባለድርሻ አካላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
en_USEN
Scroll to Top