Mols.gov.et

የዓለም አቀፉን የኢንትርፕሪነሪነርሽፕ ሳምንት ምክንያት በማድረግ …

December 6, 2023
የዓለም አቀፉን የኢንትርፕሪነሪነርሽፕ ሳምንት ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ የተሰማሩ የግል ሥራ ፈጣሪዎች በከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተጉብኝተዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢንትርፕሪነርሽፕ ልማት ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ የዓለም አቀፉን የኢንትርፕሪነሪነርሽፕ ሳምንት በተለያዩ ፕሮግራሞች እያከበረ ይገኛል፡፡ የዚህ አካል የሆነው የሥራ ፈጣሪ የግል ተቋማትን የሥራና ክህሎት፣ የኢትዮጵያ አንተርኘረነርሺኘ፣ የልማት ባንክ እና የሥኬት ባንክ የሥራ ኃላፊዎች ተዘዋውረው ጉብኝተዋል፡፡ ከተጎበኙት መካከል የኢምፓክት ጋርመንትና የህትምት መስራችና ሥራ አስኪያጅ የሆነችው ወ/ሮ ማርሸት ፀሃይ ባለፉት ዓመታት ከ15 ሺ ብር በመነሳት ዛሬ ላይ የ20 ሚሊዩን ካፒታል ማንቀሳቀስ የቻልኩት በሴቶች ኢንትርፕሪነርሽፕ ልማት ፕሮጀክት በተደረገልኝ ያላሰለሰ ድጋፍ ነው ያለች ሲሆን ከዚህ በላይ ለመንቀሳቀስ ግን የንግድ ስርዓቱን ምቹ ማድረግ ያስፈልጋል ብላለች፡፡ ሌላኛው ከ300 በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞችን የሥራ ዕድል በመፍጠር ለሃገሪቱ የማያቋርጥ የውጭ ምንዛሬ እያስገባ ያለው ኤክስለረንት ቴክኖሎጂ ሶሊሸን የተጎበኘ ሲሆን የዓለም አቀፍ የአውት ሶርሲንግ ስራን ወደ ኢትዮጵያ በስፋት እንዲገባ ከመንግስት ከፍተኛ ድጋፍ ያስፈልጋል ሲል ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ መላኩ በሻህ ገልጿል። በዚህ ጉብኝት ከተካተቱት መካከል አንዷ የሆነቸው አራያት ታምራት በእደ ጥበብ ቢዝነስ ላይ ተሰማርታ ከ80 በላይ ለሚሆኑት የሥራ ዕድል ፈጥራለች፡፡ ባህላዊ የኢትዮጵያ እሴትን ወደ ቢዝነስ የቀየረችው አራያት ከዚህ የበለጠ ለመስራት የብድር አቅራቢ ተቋማት ከተለመደው አሰራር ወጥተው ተራማጅ የሆነ አሰራር ሊከተሉ ይገባል ብላለች፡፡ በሥራ አንቀሳቃሾች በተነሱት ሐሳቦች ውይይት ያደረገው የልዑካን ቡድኑ ለፖሊሲ ግብአት የሚሆኑ ሐሳቦችንና መፍትሄ የሚሻቸውን ጥያቄዎች ለሚመለከታቸው አካላት ለማቅረብ ስምምነት ላይ ደርሷል::
en_USEN
Scroll to Top