Mols.gov.et

የዓለም ሥራ ድርጅት በኢትዮጵያ የመቶ አመት ጉዞ ላይ…

December 5, 2023
የዓለም ሥራ ድርጅት በኢትዮጵያ የመቶ አመት ጉዞ ላይ ያተኮረ እና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ የዓለም ሥራ ድርጅት አባል የሆነችበት መቶኛ ዓመት ክብረ በዓል እና የብሄራዊ የአሠሪና ሠራተኛ ጉባኤ ላይ የዓለም ሥራ ድርጅት በኢትዮጵያ የመቶ አመት ጉዞ እና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡ በፓናል ውይይቱ የዓለም ሥራ ድርጅት ዋና ማዕቀፍ የሆኑት ምቹ የሥራ ሁኔታ መፍጠር፣ የሙያ ደህንነትና ጤንነት ማረጋገጥ፣ የማህበራዊ ምክክር ባህል ማሳደግ፣ የማህበራት ማደራጀት ምጣኔ ማሳደግ፣ የሶስትዮሽ ቅንጅት ማጠናከር፣ የአማካሪዎች ቦርድ ማጠናከር እና የሠራተኞች ዝቅተኛ ደሞዝ መወሰንና ኢትዮጵያ ያላጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እንዲጸድቁ የሚሉ ሀሳበች ተነስተዋልደ የዓለም ሥራ ድርጅት ባለፉት መቶ አመታት በርካታ ሥራዎችን መስራቱን የተጠቆመ ሲሆን በተለይ የተቋማት አቅም ግንባታ በማጠናከር እና በመደገፍ በኩል የነበረው አበርክቶ ጉልህ ነበር ተብሏል፡፡
en_USEN
Scroll to Top