Mols.gov.et

የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ዙሪያ ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት…

October 19, 2025
የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሚንስትር ዴኤት ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ በህጋዊ የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ዙሪያ ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ቺፍ ኦፍ ሚሺን አቢባቱ ዋኔ ጋር ተወወያዩ። ክቡር አቶ ዳንኤል በውይይቱ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ህጋዊ የሥራ ስምሪቱን ማጠናከር ዋነኛው መፍትሄ በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የውጭ አገር የሥራ ስምሪትን አዋጅ አሻሸሎ ወደ ተግባር መግባቱን ገልፀዋል። የዜጎችን መብት ደህንነት ለማስጠበቅ ከአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ቺፍ ኦፍ ሚሺን አቢባቱ ዋኔ በበኩላቸው በፍልሰት ለስራ ወደ ተለያዩ ሃገራት ለሚሄዱ ሰራተኞች መብትን የሚያሰጠብቁ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቀረጽ የአቅም ግንባታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሚሰራው ሥራ አሰፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደርጉ አረጋግጠዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top