Mols.gov.et

የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት…

April 3, 2024
የላቀ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ለስኬት! የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የሁለት ወራት ዕቅድ አፈፃፀምን ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ በተገኙበት ገምግመናል። የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የዘርፉ ተዋንያንን ባሳተፈው በዚህ መድረክ በውጭ ሀገራት ዜጎችን ለሥራ ማሰማራት የተጀመረው ጥረት አበረታች ውጤት የታየበት መሆኑን አይተናል፡፡ ልምምዱም በቀጣይ ብቁና ተወዳዳሪ የሰለጠነ የሰው ኃይል አዘጋጅቶ ለዓለም ገበያ ከማቅረብ ባለፈ ለሀገር ውስጥ የሰው ኃይል ዝግጅትና ሥራ ስምሪታችን ጭምር ተሞክሮ ያገኘንበት እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ በአንፃሩ ህገወጥነት በየጊዜው መልኩን የሚቀያይርና አሁንም ዘርፉን እየፈተነ ያለ በመሆኑ ህጉን ጠብቀው የሚሰሩት አካላትን የሚያበረታታ እንዲሁም ህገወጦችን ተጠያቂ የሚያደረግና ከመስመር የሚያስወጣ ስርዓት ለመዘርጋት የዘርፉ ተዋንያን የጀመሩትን የተቀናጀ ሥራ አጠናክሮ ለመቀጠል መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ከዚህ በመነሳትም በቀጣይ ከሰለጠነ የሰው ኃይል ዝግጅትና አቅርቦት፣ ከመዳረሻ ሀገራት ፍላጎት እንዲሁም በሂደቱ ተሳትፎ ያላቸው ተዋንያን ሚና ጋር ተያይዞ ያሉ ዕድሎችን እና ተግዳሮቶችን በአግባቡ የለየ ዕቅድ አዘጋጅቶ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ክቡር አምባሳደር ግርማ ለሥራው ውጤታማነት እያደረጉት ላሉት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም ሚናቸውን በአግባቡ እየተወጡ ላሉ አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡ የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
Scroll to Top