የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱን የአሰራርና የቁጥጥር ስርዓቱን…
April 22, 2024
የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱን የአሰራርና የቁጥጥር ስርዓቱን በማዘመን የባለራዕይ አመራርን የሚያጣምር አጠቃላይ አካሄድ እንደሚያስፈልገው ተጠቆመ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክብርት ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ስርዓቱን በጋራ ማሳለጥ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸው ዜጎች ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት እንዲያገኙ፣ መብትና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ እና የአመራር ሥርዓቱን እና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የተጀምሩ ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡
በዘርፉ የተደረገውን ሪፎርም ተከትሎ ዜጎች መብትና ደህንነታቸው እንዲሁም ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ሁሉም የሚመለከተቻው አስፈፃሚ አካላት በጋራ እየሰሩ ያሉትን ተግባራት በማጠናከር የአሰራርና የቁጥጥር ስርዓቱን በማዘመን የባለራዕይ አመራርን የሚያጣምር አጠቃላይ አካሄድ እንደሚያስፈልግ በውይይታቸው ላይ አንስተዋል፡፡
የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የምልመላ ሂደቱን ለማሳለጥ፣ግልጸኝነትን ለማጎልበት እና በውጭ ሀገር ያሉ ዜጎችን ደህንነት በማረጋገጥ ከብልሹ አሰራር የፀዳ አገልግሎት ለመስጠት ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሂደት በየደረጃው ያሉ አመራሮች ወሳኝ ሚና እንዳላቸውም ተመልክተዋል።
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በኢትዮ ቴሌኮም መካከል የተጀመረው የቅንጅት ሥራን አጠናክሮ በማስቀጠልና ካለፈው ልምድ በመውሰድ የዜጎችን መብትና ደህንነት እንዲሁም ተጠቃሚነት በአግባቡ እንዲረጋገጥ በትኩረት ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል፡፡