Mols.gov.et

የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ …

March 21, 2024
የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ በክህሎት ልማቱ ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳወቀ፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (KOICA) ም/ል ፕሬዚዳንት ዶንግ ሆ ኪም የተመራ የልዑካን ቡድን ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ ኮይካ በኢትዮጵያ የክህሎት ልማቱን ለመደገፍ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እና የቀጣይ የትብብር መስኮችን ተመልክተዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስት ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያና ኮሪያ የቆየ የወዳጅነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው፡፡ ኮይካ በኢትዮጵያ የክህሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ እየሰራ ያለው ሥራ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው ብለዋል፡፡ በክህሎት ልማቱ ዘርፍ የተጀመሩ አበረታች ሥራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባ የጠቀሱት ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በቀጣይ በሚኖረው የትብብር መስክ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉ እንዲካተት ጠይቀዋል፡፡ የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (KOICA) ም/ል ፕሬዚዳንት ዶንግ ሆ ኪም በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያና ኮሪያ ያላቸውን የወዳጅነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማሳደግ እንፈልጋለን፡፡ ኤጀንሲው በክህሎት ልማቱ ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍም አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ከክህሎት ልማት ባለፈም በእውቀትና ቴክኖሊጂ ሽግግር እንዲሁም በሥራ ዕድል ፈጠራው ዘርፍም በትብብር የምንሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡ ከውይይቱ በኋላ የልዑካን ቡድኑ በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጉብኝት አድርገዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top