Mols.gov.et

የክህሎቶች ልማት፤የአፍሪካ ቀጣይ የእድገት ምዕራፍ እና ግንባር

October 16, 2025
የክህሎቶች ልማት፤የአፍሪካ ቀጣይ የእድገት ምዕራፍ እና ግንባር አፍሪካ የተስፋ እና የበረከት አህጉር ብቻ አይደለችም የዓለም ቀጣይ የእድገት ዳርቻ እና ማዕከል ጭምር እንጂ።ህዝቧ እ.አ.አ በ2024 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተሻግሯል፤ እ.አ.አ በ2050 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከአንድ ትውልድ በኋላ ባለንባት ምድር ላይ ከአራት ሰዎች መካከል አንዱ ከአፍሪካ እንደሚሆን ይጠበቃል።በጣም አስገራሚው ነገር ከ60 በመቶ በላይ አፍሪካውያን እድሜያቸው ከ25 ዓመት በታች ሲሆን ይህም አፍሪካን ወጣቷ አህጉር አድርጓታል። ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ወጣት ትልቅ የስነ ህዝብ ትሩፋት ነው። ይህን አቅም ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ከተቻለ አፍሪካን የዓለም ክህሎት መፍለቂያ፣ የፈጠራ እና ኢኖቬሽን ማዕከል ማድረግ ይቻላል። ይሁንና የስነ ህዝብ ትሩፋት ብቻውን ልማት እንዲረጋገጥ አያስችልም። እውነተኛው ፈተና ያለው ይህን የተትረፈረፈ የሰው ሀብት በክህሎት የዳበረ፣ ለተለዋዋጭ ሁኔታዎች ራሱን ብቁ ያደረገ እና መፍጠር ወደ ሚችል የስራ ኃይል መቀየር ላይ ነው። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የሰው ኃይል “የምንፈልጋትን አፍሪካ ለመፍጠር” የሚያስችል ዋንኛ ምሰሶ እንደሆነ ያስቀምጣል። ይህ አህጉራዊ ማዕቀፍ በእውቀት እና ሁሉን አቀፍ እድገት አማካኝነት የበለጸገች፣ የተሳሰረች እና ራሷን የቻለች አህጉርን የመፍጠር ራዕይን አንግቧል። አፍሪካ የሰው ሀብት ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ሀብቶች ባለጸጋም ናት። አፍሪካ የዓለማችን 30 በመቶ የማዕድን ሀብት የሚገኝባት አህጉር ናት። ኮባልት፣ ሊቲየም፣ ፕላቲኒየም እና ሌሎች ውድ ማዕድናትን በስፋት ይገኙበታል። ማዕድናቱ አሁን ዓለም ላለችበት አረንጓዴ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ቁልፍ የሚባሉ ናቸው። የዓለማችን 60 በመቶ ያልታረሰ መሬት ያለው በዚችሁ አህጉር ነው። ይህ እርሻ የማያውቀው መሬት የዓለምን የምግብ ስርዓት በከፍተኛ ሁኔታ የመቀየር አቅም አለው። ከ10 ቴራ ዋት በላይ የፀሐይ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላት አፍሪካ ከአህጉር አልፋ የኢንዱስትሪ እና ዲጂታል መሰረተ ልማቶችን በኃይል የማመንበሽበሽ አቅም አለው። የኢኮኖሚ ማዕበሉም ወደ አፍሪካ ያደላ ይመስላል። እ.አ.አ 2021 ገቢራዊ መሆን የጀመረው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና 55 ሀገራትን የሚያስተሳስር እና 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተጠቃሚን በአንድ ማዕቀፍ ስር የሚያሳባስብ ነው። በአህጉር ደረጃ ዓመታዊ ጥቅል ምርቱ (ጂዲፒ) 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ይገመታል እንደሚገመት ጠቅሶ የዘገበው ኢዜአ ነው።
en_USEN
Scroll to Top