Mols.gov.et

የእንቆጳ ጉባኤ(Enkopa Summit) በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡

October 6, 2023
የእንቆጳ ጉባኤ(Enkopa Summit) በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በዲጅታል ኢኮኖሚ ያላትን እምቅ አቅም ለመጠቀም እና መንግስትና የግሉን ዘርፍ በማስተሳሰር የሥራ ፈጣሪነት ምህዳርን ለማስፋት ያለመ እንቆጳ ጉባኤ(Enkopa Summit) በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ጉባኤው በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ከጥቅምት 1 ¬- 2/2016 ዓ.ም ነው የሚካሄደው። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን መድረኩን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት መድረኩ የዘርፉ ተዋናዮች በማስተሳሰር በኢትዮጵያ የኢንተርፕረነርሺፕ ስነ-ምህዳር ለማስፋት እና በድጅታል ኢኮኖሚ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ አቅም ለተቀሪው ዓለም ለማስተዋወቅ የሚስችል ነው፡፡ በመድረኩ የዘርፉ ምሁራን፣ፖሊሲ አውጪዎች፣ አህጉራዊ ተቋማት፣ አለም አቀፍ ኮርፖሬሽኖች፣ የልማት አጋር አካላት፣ የግሉ ዘርፍ ተወካዮች፣ሥራ ፈጣሪዎች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት፣ ኢንቨስተሮች፣ በፍሪላስንጊ እና ጊግ ኢኮኖሚ በንቃት የሚሳተፉ የግል ድርጅቶች፣ ስታርታፖችን ጨምሮ የ26 ሀገራት ተወካዮች በጉባኤው ይሳተፋሉ፡፡
en_USEN
Scroll to Top