Mols.gov.et

Project

የኢፌዴሪ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራችንን ለማሳረፍ ለኮሚሽናችን በአደራ በተሰጠን የመትከያና የመንከባከቢያ ቦታ ለ3ኛ ዓመት 200 ችግኞች ተክለናል። ቀድመን የተከተልናቸውና ስንንከባከባቸው የቆዩ ችግኞችም በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።

Nov 16 , 2021 

የኢፌዴሪ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራችንን ለማሳረፍ ለኮሚሽናችን በአደራ በተሰጠን የመትከያና የመንከባከቢያ ቦታ ለ3ኛ ዓመት 200 ችግኞች ተክለናል። ቀድመን የተከተልናቸውና ስንንከባከባቸው የቆዩ ችግኞችም በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። በችግኝ መትከያ ቦታችን አዋሳኝ ሰፈር ውስጥ የሚኖሩ 3 ህጻናት ለሁለተኛ ዓመት በበጎ ፈቃዳቸው፣ የራሳቸውን የአፈር መኮትኮቻ ይዘው፣ ማልደው ተቀላቅለውናል። ህጻናቱ ከስር ከስር ችግኞቹ የመጡበትን የፕላስቲክ (ፌስታል) መትከያ በመሰብሰብ ምን ያህል ጠንቃቃ ትውልድ እንደሆኑ አስመስክረዋል። አሻራችን በመሬቱና በአፈሩ ላይ ብቻ ሳይሆን በትውልዱ ላይም ሊሆን ስለሚገባ ፤ ዘለቄታ ያለውና አመርቂ የሥራ ዕድሎች ለሁሉም እንዲዳረሱ የምንሰራው ሥራ ለተተኪው ትውልድ መሰረት የሚጥልና ህይወትን የሚያሻሽል መሆን እንዳለበት በይበልጥ አጽንተን ተመልሰናል።
en_USEN
Scroll to Top