Mols.gov.et

የኢንዱስትሪ ማህበረሰብ ምክክር …

March 14, 2024
የኢንዱስትሪ ማህበረሰብ ምክክር የሁሉንም ወገኖች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁነኛ መፍትሄ ነው። ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የአሠሪና ሰራተኛ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ያዘጋጀው የኢንዱስትሪ ማህበረሰብ ምክክር ለምርታማነት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ፤ የኢንዱስትሪ ማህበረሰብ ምክክር አሠሪም ይሁን ሠራተኛ በአጠቃላይ የሁሉንም ወገኖች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁነኛ መፍትሄ ነው። በቀጣይ በኢንዱስትሪው ማህበረሰብ በየደረጃው በትኩረት በሚከናወኑ ምክክሮች የዘርፉ ተግዳሮቶችን ነቅሶ ለማውጣት፣ ለዘርፉ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት እና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ አዲስ የኢንዱስትሪ ባህል ለመገንባት መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል። በሚኒስቴሩ የኢንዱስትሪ ግንኙነትና ሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ርተካልኝ አያሌው በበኩላቸው፤ ተግባራዊ የሚደረገው ምክክር የሚኒስቴሩ የሪፎርም አጀንዳ አካል መሆኑን ገልጸው ምክክሩን ፍሬያማ ለማድረግ ገለልተኛ የሆኑ አመቻቾች የማሰልጠን ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። መድረኩ ለቀጣይ ሦስት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን የምክክሩ አመቻቾች እና አስተባባሪዎች አቅም የሚያሳድጉ እና ግንዛቤ የሚያሰጨብጡ ስልጠና ይሰጣል አካላት ይሰጣል። በመጀመሪያ ዙር ስልጠና ከ83 ደርጅቶች የተወጣጡ 400 የሚሆኑ ተሳታፊዎች በመድረኩ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
en_USEN
Scroll to Top