“የኢንዱስትሪ ማህበረሰብ ምክክር ለምርታማነት”
በኢንዱስትሪ ማህበረሰብ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ አዲስ የኢንዱስትሪ ባህል ለመገንባት ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀው የምክክር ማስጀመሪ የአመቻችነት እና አስተባባሪዎች ስልጠና እንደቀጠለ ይገኛል።
ከአሰሪ፣ ሰራተኛ፣ ማህበራት፣ ፌዴሬሽኖች እና መንግስት የተውጣጡ አካላት እተሳተፉበት በሚገኘው በዚህ ስልጠና በሁለተኛ ቀኑ የምክክሩ አመቻቾች እና አስተባባሪዎች ወደ ኢንዱስትሪ ሲመለሱ ፍሬያማ ምክክር ማድረግ የሚያስችላቸውን የአቅም ግንባታ ስልጠና በኢትዮጵያ ኢንተርኘረነርሺኘ ኢንስቲትዩት እየተሰጠ ይገኛል።