Mols.gov.et

የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ አመራሮች ካውንስል ተመሠረተ

May 29, 2024
የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ አመራሮች ካውንስል ተመሠረተ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በምስረታው መርሃ ግብር ላይ እንደተናገሩት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለሀገራዊ ልማት በመካከለኛ^^ና ዝቅተኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ሃይል በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። ተቋማቱ የክህሎትና የዕውቀት ሽግግር በማድረግ ተልዕኳቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ተመሳሳይ ተልዕኮ ካላቸው ተቀማት ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተደራጀ መልኩ ለማሳለጥ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ዘርፉን ማስተሳሰር የሚያስችል የቴክኒክና ሙያ አመራሮች ካውንስል “ብቁ መሪነት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ሃሳብ በይፋ መመስረቱን ገልጸዋል፡፡ ካውንስሉ ተቋማቱ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት እንዲወጡ እንዲሁም ስራቸውን ተናበው የሚሰሩበት ወጥ የሆነ የአደረጃጀት ስርዓት መገንባት የሚያስችላቸው መሆኑን ተናግረዋል። የአመራር ካውንስሉ ጥናትና ምርምር በማድረግ ልዩነት መፍጠር የሚችል የሰው ኃይል ማፍራት ይጠበቅበታል ብለዋል። ካውንስሉ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ገበያ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ከማፍራት አንጻር ከምንጊዜውም በላይ ፍጥነትን፣ ፈጠራን፣ ጥራትንና ብዛትን ማዕከል አድርጎ እንዲሰራ አሳስበዋል። የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ብሩክ ከድር በበኩላቸው በኢትዮጵያ ከ2ሺህ በላይ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት በመንግሥትና በግል ባለቤትነት ስራ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ከእነዚህም መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑት የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ኮሌጆቹ የበርካታ ወጣቶችን ክህሎት በማበልጸግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ስራ እያከናወኑ መሆኑን አንስተዋል። የበለጸገ ክህሎት የማስጨበጥ ስራው በተለይ ወጣቶች ከራሳቸው ባለፈ ለሀገራቸው ኢኮኖሚ የማይተካ ሚና እንዲጫወቱ እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል።
en_USEN
Scroll to Top