Mols.gov.et

የኢትዮጵያ-ቻይና ከፍተኛ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አመራሮች ዓመታዊ ውይይት መካሄድ ጀመረ።

August 30, 2025
የኢትዮጵያ-ቻይና ከፍተኛ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አመራሮች ዓመታዊ ውይይት መካሄድ ጀመረ። የኢትዮጵያ-ቻይና የ2025 የቴክኒክና ሙያ አመራሮች የውይይት መድረክ በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከሁለቱ አገራት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የተውጣጡ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል። ውይይቱን የከፈተቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዲኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር)፣ በቤጂንግ ጉባዔ በቻይና-አፍሪካ ትብብር የተያዘውን የጋራ ራዕይ ተግባራዊ ለማድረግ ይህ ውይይት ዋጋው ከፍ ያለ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ አገራዊ ዕድገትን ለማፋጠን፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና ለሁለንተናዊ ብልጽግና ወሳኝ መሆኑን በማመን በትኩረት እየሰራች ነው ያሉት ዶ/ር ተሻለ በዘርፉ ቻይና ያለፈችባቸውን ልምዶች እንማርባቸዋለን ብለዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘውም ይህ የውይይት መድረክ ትልቅ ውጠየት እንደሚመጣ ገልፀው በጋራ ሥንሰራ ለሁለቱ አገራት ብቻ ሳይሆን ለቻይና-አፍሪካ ትብብር ውጤት እናመጣለን ብለዋል፡፡ የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ አዋቶ በበኩላቸው የሁለቱ አገራት ትብብር በሉባን ወርክሾፕና በኮንፊሼሽ ኢንስቲትዩት የክህሎት ስልጠና ዘርፎች ተጠናክሮ እንደቀጠለ ገልጸዋል። የሁለቱ አገራት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ከፍተኛ ሃላፊዎች የሚያደርጉት ውይይት በተቋም አመራር ልምድን በማጋራት፣ ስልጠናዎችን ከዓለምአቀፍ ሁኔታ ጋር በማጣጣም፣ የቴክኖሎጂና የሰው ሃይል ልውውጥን በማድረግ ከዘርፉ የሚጠበቀውን ውጤት ከፍ ያደርጋል ብለዋል። በውይይቱ የሚሳተፉ የቻይና ተቋማት ሃላፊዎችን የመሩት የቻይና ዓለምአቀፍ ህዝብ-ለህዝብ ልውውጥ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዩ ቻንግዡ፣ የቤጂንጉን ቻይና -አፍሪካ ጉባዔ መነሻ በማድረግ የብሪክስ አባል አገራት ባደረጉት የክህሎት ውድድር ኢትዮያ ተሳትፋ ማሸነፉዋን አስታውሰው በክህሎት ልማት ዘርፍ እየመጣ ያለውን ውጤት ማሳያ አድርገው ተናግረዋል፡፡ ዛሬ እየተካሄደ ያለው ውይይትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ከሁለቱ አገራት ከፍተኛ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የተውጣጡ አመራሮች ዘላቂ ትብብርን አጠናክሮ በማስቀጠል እና በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ በሚደረጉ ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ነው።
en_USEN
Scroll to Top