Mols.gov.et

የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦች የሚያስተዋውቅ ፌስቲቫል ..

October 8, 2025
የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦች የሚያስተዋውቅ ፌስቲቫል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋም የሆነው ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ የሚገኙ ባህላዊ የምግብ አይነቶች በሆቴሎች የምግብ ሜኑ ዝርዝር ውስጥ እንዲካተቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በጥናት ለይቶ ያቀረባቸው 31 የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ የምግብ ፌስቲቫል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ፣በኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ አስተዳደር ከኩሪፍቱ አፍሪካ ቪሌጅ ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል ። ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የባህላዊ ምግቦች ፌስቲቫል ጥቅምት 1/2018 የኢትዮጵያውያንን ባህላዊ ምግቦች ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅ ትልቅ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መስከረም 28/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
en_USEN
Scroll to Top