Mols.gov.et

የአፍሪካን ኢንዱስትሪያላይዜሽን ለማፋጠን ወጣቶችን በክህሎት ማነጽ እንደሚገባ ተጠቆመ

April 30, 2024
የአፍሪካን ኢንዱስትሪያላይዜሽን ለማፋጠን ወጣቶችን በክህሎት ማነጽ እንደሚገባ ተጠቆ ስድስተኛው የአፍሪካ የተግባራዊ ሳይንስ፣ የምህንድስና እና የኢንጂነሪንግ (PASET) አጋርነት ፎረም በኬንያ ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ የአባል ሀገራቱ የትምህርትና ሥልጠና ሚኒስትሮች፣ አጋር እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል፡፡ በዚህም የአፍሪካን ኢንዱስትሪያላይዜሽን ለማፋጠን የቴክኒክና ሥልጠና ተቋማት የማይተካ ሚና እንዳላቸው እና ወጣቶችን በክህሎት ማነጽ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በመድረኩ ላይ በተወካያቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፣ በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የኢኮኖሚ እድገት እውን በማድረግ ሁሉን አቀፍ እድገት ለማስመዝገብ የአፍሪካን ወጣቶች በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በምህንድስና ማነጽ ይገባል። በአሁጉሪቱ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት፣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እና ለበርካታ የሰው ሃይል የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና የሚታሰበውን ኢንዱስትሪያላይዜሽን እውን ለማድረግ የክህሎት ስልጠና የማይተካ ሚና ይጫወታል፡፡ ስለሆነም አፍሪካን ወደ አዲስ የኢንዱስትሪ የዕድገት ምዕራፍ ለማሸጋገር ለክህሎት ልማት ልዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በመድረኩ የፎረሙ አባል ሀገራት ከክህሎት ልማት እና ከሥራ ዕድል ፈጠራ አኳያ ያላቸውን ልምድና ተሞክሮሯቸውን አካፍለዋል፡፡ ፎረሙ ኢንትዮጵያን ጨምሮ 12 ሀገራትን (ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ሴኔጋል፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ሞዛምቢክ፣ ቤኒን፣ ታንዛኒያ፣ ሶማሊያ እና ቡርኪናፋሶ) በአባልነት ያቀፈ ነው፡፡
en_USEN
Scroll to Top