Mols.gov.et

የአይሶ(ISO) 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ።

May 15, 2024
የአይሶ(ISO) 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፀድቆ ተግባራዊ የሚደረገው የጥራት ሥራ አመራር አገልግሎት ISO 9001:2015 በእያንዳንዱ የሥራ ክፍል የሚከናወኑ ተግባራትና አሰራራቸው በቅደም ተከተል የመለየት ሥራ ተከናውኗል። በዚህም በተቀመጠው የጥራት የደረጃ አግባብ ለመተግበር እና ለማስተግበር ከፍተኛ የአመራር ቁርጠኝነት አለ ብለዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ነቢሃ መሀመድ በበኩላቸው ተግባራዊ የሚደረገው የጥራት ጀረጃ በሚኒስቴሩ የሚሰጡ አገልግሎቶች ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ የተገልጋይ እርካታ የሚያሳድግ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ገልጸው ለዚህም 576 የሚሆኑ የጥራት ደረጃ ሰነዶችን በማዘጋጀት ለትግበራ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። በመድረኩ የተገኙት የየዘርፉ ሚኒስትር ዴኤታዎች ስርዓቱ በአግባቡ ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውንም ገልጸዋል። በመድረኩ ላይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥራ ላይ አስተዋጽዎ ያበረከቱ አመራርና ባለሙያዎች እውቅ ተሰጥቷቸዋል።
en_USEN
Scroll to Top