Mols.gov.et

የአማራ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት…

September 29, 2025
የአማራ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በክቡር ርእሰ መሥተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት – የልህቀት ብስራት በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሃ ግብር አስር የክልል ቢሮዎች እና አራት ከፌዴራል ተቋማት 42 የሚሆኑ ገልግሎቶች ወደ ሥራ ይገባሉ፡፡ ወደ ሥራ ከገባው የባህዳር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በተጨማሪም በደሴ እና በጎንደር ማዕከላቱ እየተፋጠኑ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ካስገባቸው አገልግሎቶች መካከል የውጭ ሀገር ዜጎች የሥራ ፍቃድ አገልግሎት ይገኝበታል፡፡ በዚህም የሥራ ፍቃድ ዕድሳት፣ የሥራ ፈቃድ መተካት እና የሥራ ፈቃድ ክሊራንስ የሚሰት ሲሆን የኦንላየን የኢንተርፕራይዝ ምስረታ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል፡፡ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በተለያዩ ተቋማት የሚሰጡ የመንግስት አገልግሎቶች ወደ አንድ ማዕከል በማምጣት ፈጣን፣ ቀልጠፋ እና ምቹ አገልግሎት ለዜጎች ለመስጠት ወደ ስራ የገባ ማዕከል ነው፡፡
en_USEN
Scroll to Top