Mols.gov.et

የአላጌ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ አመራርና ሠራተኞች …

July 31, 2025
የአላጌ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ አመራርና ሠራተኞች በኮሌጁ እና በኮሌጁ አካባቢ በሚገኙ አጎራባች ክልል ዞን እና ቀበሌዎች የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ የአካባቢን ስነ-ምህዳር ከሚጠብቁ ችግኞች በተጨማሪ ከ32 ሺህ በላይ የፍራፍሬ ችግኞችን መትከል መቻሉን የኮሌጁ ዲን ረዳት ፕሮፌሰር መርክነህ መሰኔ ገልፀዋል፡፡ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኮሌጁ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ባራ እና ናቃ ቀበሌዎች እንዲሁም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ ከ10 ሄክታር በላይ በሚሆን መሬት ላይ የፓፓያ እና የሞሪንጋ ችግኝ መተከሉንም አመላክተዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top