የቻይና አፍሪካ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ልምድ ልውውጥ ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ” የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር የተደረገው ስምምነት ወደ ተግባር የተገባበት መሆኑን እና ቻይና በሰው ሃይል ልማት በቴክኖሎጂ ሽግግርና በመምህራን ስልጠና ድጋፏን እያጠናከረች ነው ብለዋል።”
በመርሀግብሩ ላይ የቻይና አፍሪካ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ጥምረት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማርክ ጎንግ ዙዉ ; ለቻይና እድገት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ትልቅ ሚና እንደነበረው በመጥቀስ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገትና ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉ ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።
ቻይና በአፍሪካ ሩዋንዳ፤ ታንዛኒያ፤ ኢትዮጵያ እና ሌሎች ሀገራት ላይ ዘርፉን ለማሳደግ ከአቅም ግንባታ ስልጠና ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ስታደርግ ቆይታለችም ብለዋል።
በተለይም ኢትዮጵያና ቻይና የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸውና በኢኮኖሚና በመሰረተ ልማት በግብርናው መስክ በጋራ ሲሰሩ መቆየታቸውን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ በቴክኒክና ሙያ መስክም ቴክኖሎጂዎችን ማሸጋገርን ጨምሮ የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጠች ነው ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።