Mols.gov.et

የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ተልዕኮ…

December 13, 2023
“የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ተልዕኮ ለማሳካት ሃሳብ ያለማቋረጥ የሚፈልቅበት አደረጃጀት ፈጥሮ መጓዝ ወሳኝ ነው፡፡ ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል“ የሥራና ክህሎት ሚንስትር ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ በፖሊሲ አተገባበርና በጥናትና ምርምር ሥራዎች ላይ የካበተ ልምድ ያላቸው ምሁራን የተሰባሰቡበት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ላይ የሚመክር እና ሃሳብ የሚያመነጭ የቲንክ ታንክ በድን ምስረታ ተካሄደ ፡፡ በምስረታ መድረኩ ላይ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚንስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት፤ ቡድኑ ሃሳብ ያለማቋረጥ የሚፈልቅበት አደረጃጀት ፈጥሮ ለመጓዝ እና በፖሊሲ አተገባበር ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት፣ ልምድና ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ ትልቅ አስተዋጽዎ ያበርክታል፡፡ የቲንክ ታንክ ቡድኑ መቋቋም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት ስኬታማ ለማድረግ እና ዘርፉ ባልተቋረጠ ጥናትና ምርምር እንዲሁም በተደመረ እውቀት ለመምራት ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረውም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ የኢፈዴሪ የቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በበኩላቸው ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ብቁ፣ የሰለጠኑ፣ ሀገራቸውን የሚወዱ ዜጎች የምናፈራበት በመሆኑ የዘርፉ ሙሁራን እውቀትና ልምድ መጠቀም ዘርፉን ወደ ፊት ለማሻገር እና ተግዳሮቶችን ለመፍታት ይረዳል ብለዋል፡፡ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ መድረክ የተለያዩ ዘርፉን የሚመለከቱ ጥናቶች እና ጽሁፎች እየቀረቡ ምክክር እየተካሄደ ይገኛል፡፡
en_USEN
Scroll to Top