Mols.gov.et

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር ……

February 2, 2024
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር … በጀርመን ቆይታችን በደቡባዊ ባቫሪያ በምትገኘው ጥንታዊቷ ዌልሃይም ከተማ የሚገኙትን የሕዝብ የሙያ ማሰልጠኛ ተቋምን፣ የዕደ-ጥበብ ማዕከልን እንዲሁም በኢኖቬቲቭና ጊዜውን የዋጀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የሚታወቀውን ኤፌ ባወር የቤተሰብ ትውልድ ተሻጋሪ ድርጅት ጎብኝተናል፡፡ በሥራ ጉብኝታችን በትምህርትና ስልጠና ተቋማት እና በኢንዱስትሪው መካከል ጠንካራ ግንኙነት መፍጠር ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያ ለማፍራትም፣ አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንም ሆነ ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል ያለውን ሁለንተናዊ ፋይዳ ተመልክተናል፡፡ በማሰልጠኛ ተቋማትና በኢንዱስትሪዎች መካከል በሚፈጠር ጠንካራ ግንነት የሚሰጠው የሁለትዮሽ የትብብር ስልጠና ሰልጣኞች ከንድፈ ሀሳብ ያለፈ በተግባር እውቀትና ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበት ዕድልን የሚፈጠርላቸው እንደሆነም አይተናል፡፡ ይህም በየሙያ መስኩ ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያ ለማፍራት አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ወሳኝ መሆኑን ከግምት በማስገባት እንደ ሀገር የጀመርናቸውን ሥራዎች አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል፡፡ ይህ የሥራ ጉብኝት በዘርፉ ለጀመርናቸው ተስፋ ሰጪ የሪፎርም ሥራዎቻችን ግብዓት የሚሆኑ ልምድና ተሞክሮዎችን ያገኘንበትና በብዙ ያተረፍንበት ነው፡፡ ስለሆነም መርሃ ግብሩን ላመቻቹልን እና ተሞክሮዎቻቸውን ላካፈሉን አካላት በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡
en_USEN
Scroll to Top