Mols.gov.et

“የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በኢንተርፕሪነርሺፕ …

January 2, 2024
“የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በኢንተርፕሪነርሺፕ እሳቤ የተቃኙ እንዲሆን ለማስቻል በትኩረት እየሠራን ነው።” ክቡር ዶ/ር ተሸለ በሬቻ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ የቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከላትን (Business Incubation Center) በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት በማስፋፋት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡ የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በኢንተርፕሪነርሺፕ እሳቤ የተቃኙ እንዲሆን ለማስቻል በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ችግርን ወደ ዕድል የመቀየርና አዳዲስና ፈጠራ የታከለባቸው ሃሳቦችን የማፍለቅ አቅም እንዲኖራቸው የሚያስችሉ ተግባራት በሚኒስቴር መ/ቤቱ እየተከናወኑ እንደሚገኙ የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በማሰልጠኛ በተቋማት ውስጥ የቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከላትን ማቋቋም አንደ አንድ ስልት የተወሰደ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የኢንተርፕሪነርሺፕ ሥነ- ምህዳር በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ ለማስፋት፣ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዕውን እንዲሆን ለማስቻል፣ በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛና በቢዝነስ ተቋማት መካከል ትስስር ለመፍጠር እና ለምሩቃን ምቹ የሥራ ዕድልን ለመፍጠር የቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከላቱን መደገፍና ማሳደግ ወሳኝ ተግባር መሆኑንም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል፡፡ በቀጣይም ውጤታማ የሆኑ የቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከላትን በመላ አገሪቱ በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ለማስፋፋት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በጥምረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢንጆይ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ የቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከላትን በማቋቋምና ውጤታማ በማድረግ አንፃር የተገኙ የተለያዩ ተሞክሮዎችና ማዕከላቱን በቀጣይ መስፋትና ማሳደግ የሚያስችሉ ገለፃዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top