Mols.gov.et

” የተቀናጀ የሙያ ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ…

November 30, 2023
” የተቀናጀ የሙያ ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ ሥርዓቱ የሥልጠና ጥራቱን ለማስጠበቅ ካለው ፋይዳ ባሻገር የዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡ “ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሙያ ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ ስርዓቱን ለማዘመን እየተከናወኑ ባሉ የሪፎርም ሥራዎችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ከክልል የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደረገ፡፡ በበይነ መረብ በተካሄደው በዚህ ውይይት ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ በውይይቱ በቅርቡ በልጽጎ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነው የተቀናጀ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ስርዓት አተገባበር፣ የመደበኛና አጫጭር ስልጠና አጠናቃቂዎችን ብቃታቸውን በምዘና የማረጋገጥ አፈፃፀምና የገጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም በሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክፍተት ምክንያት በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ ላይ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽዕኖ እና እሱን ለመቀነስ መወሰድ ስላለባቸው የእርምት እርምጃዎች ላይ ጥያቄዎች ተነስተው ማብረሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ በዘርፉ የሥልጠና ጥራትና አግባብነትን ለማረጋገጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም ሀገራዊ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ስርዓቱ ወጥነት ያለውና በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ የተቀናጀ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ስርዓት ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል፡፡ ሥርዓቱ የሥልጠና ጥራቱን ለማስጠበቅ ካለው ፋይዳ ባሻገር በዘርፉ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረት የሚያግዝና የዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ በሁሉም ክልል ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በበኩላቸው የተቀናጀ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ስርዓቱ በዘርፉ ወጥነት ያለው የአሰራር ስርዓት እንዲሰፍን እንድል የሚፈጥር ነው፡፡ ከዚህ ባለፈም ሀሰተኛ ማስረጃን መከላከል የሚያስችል እና በየዓመቱ ለሰርተፊኬት ህትመት የሚወጣውን ከፍተኛ በጀት የሚቀንስ ነው ብለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top