Mols.gov.et

የቤተሰብ ንግድ ለማህበረሰባዊ ለውጥ

August 31, 2023
ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዳዲስ እሳቤዎች መካከል አንዱ የሆነው የቤተሰብ ንግድ(family business) አስመልክቶ ለአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ አስተባባሪዎች እና ለገጠር የሥራ እድል ፈጠራ ዳይሬክሮች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡ የዓለም አቀፍ ተሞክሮ እንደሚያሳየው የቤተሰብ ንግድ(family business) ለማህበረሰባዊ ለውጥ እና እድገት የማይተካ ሚና እንደሚጫወት ይታወቃል፡፡ ሥራ ፈላጊ የሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባላት አደራጅቶ ወደ ስራ ማስገባት ሥራው ከትውልድ ወደ ትውልድ ማሸጋገር የሚችልና ውጤታማ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ የህብረተሰቡን ውስን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም እና መንግስታዊ ድጋፎችን ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል፡፡ በተጨማሪም በመድረኩ የሥራ ዕድል ፈጠራ አፈጻጸም ጋይድ ላይን እና የእሴት ሰንሰለትን መሰረት ያደረገ የገጠር የሥራ ዕድል ፈጠራ የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ይፈጠራል፡፡
en_USEN
Scroll to Top