Mols.gov.et

የባለድርሻ አካላት ጥምረት ለላቀ ስኬት ! …

February 20, 2024
የባለድርሻ አካላት ጥምረት ለላቀ ስኬት! የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተግባራችንን ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በየወሩ በጋራ ለመገምገም በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የጥር ወር ዕቅድ አፈፃፀማችንን ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ በተገኙበት ገምግመናል። በዚህም የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የዜጎቻችንን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅምን ባስጠበቀ መልኩ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በተደረገው ጥረት በጥር ወር 38,570 እንዲሁም ከነሐሴ – ጥር ባሉት 6 ወራት ከ189,830 በላይ የሚሆኑ ስልጠና የወሰዱ ዜጎችን ለሥራ ማሰማራት ችለናል። በመድረኩ ብቁና የሰለጠነ የሰው ሃይል ለማቅረብ ተግዳሮት የሚሆኑ ጉዳዮችንና የሚፈቱበትን አግባብ፣ ከፍላጎት አኳያ ያሉ ዕድሎችን አሟጦ ለመጠቀም እና አፈፃፀሙን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማሻሻል የምንችልባቸውን ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል። የዜጎቻችንን መብት፣ ደህንነትና ጥቅም በማስጠበቅ እና የሃገራችንን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ እያደገ ለመጣው የሥራው አፈፃፀም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ውጤታማ ስራዎችን ማከናወናቸውን ተመልክተናል። ለዚህም ክቡር አምባሳደር ግርማ ለሥራው ውጤታማነት እያደረጉት ላሉት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም ለሁሉም አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡
en_USEN
Scroll to Top