Mols.gov.et

የቀጣይ የኢትዮጵያ የስታርት አፕ” ማዕቀፍ ወይም በእንግሊዝኛው Next Ethiopian Startup – NEST

October 24, 2023
የኢኖቬሽን እና የኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ባህል የሚገነባበት፣ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ እምቅ አቅም ያላቸው ወጣቶች ሃሳባቸውን የሚያበለፅጉበት፣ ከመቀጠር አልፈው ሥራ የሚፈጥሩበት፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንም ከሃገር ውስጥ ባለፈ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነትን የሚያዳብሩበት፣ በተቋማት እና ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን መስተጋብር የሚያሳልጥ፣ የድግግሞሽ ሥራን የሚያስቀር፣ ለሥራ ፈጣሪዎች እና ኢንተርፕርነሮች የተሻሉ እና የተናበቡ አገልግሎቶችን የሚያመቻች፣ የአፍሪካ እና የዓለማችን ሃገሮች ላይ እንዳሉት ሥራ ፈጣሪዎች ዩኒኮርን /Unicorns (የ1 bilion ዶላር ቫሊዌሽን ያላቸው ስታርታፖች)/ ማፍለቅ የሚቻልበት እንዲሁም ላቅ ያሉ የኢኮኖሚ ፋይዳዎችን በውስጡ ያነገበ ልዩ ኢንሼቲቭ ነው። ይሄ ኢንሼቲቭ እንዲሳካ ላለፈው አንድ ዓመት ገዳማ የኢንቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚንስቴር እና የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ሆነን የቅደም ዝግጅት ስራዎችን ስናዘጋጅ ቆይተናል። በማብሰሪያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው የስራ መመሪያ ለሰጡን ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን አክብሮቴንና ምስጋናዬን እገልጻለሁ። የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ሚንስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ለሰጡት አመራር እንዲሁም በሂደቱ ለተሳተፉት የሶስቱም ተቋማት የስራ ሃላፊዎች እና ሞያተኞች ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት !
en_USEN
Scroll to Top