Mols.gov.et

የሰልጣኞች ቅበላ መጀመሩን የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ

October 29, 2024
ሰልጣኞች ቅደበላ መጀመሩን የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የሰልጣኞች ቅበላን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም በአስተዳደሩ 6 የግል እና 2 የመንግስት ኮሌጆች ሰልጣኝ ተማሪዎችን ለመቀበል ሙሉ ዝግጅቶች የተጠናቀቁ ሲሆን ሰልጣኝ ተማሪዎች ከምዝገባ በፊት የትምህርት ዘርፎችን የመለየት ሥራ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡ አስተዳደሩ የኢንዱስትሪ ማዕከል እንደመሆኑ የዲጂታላይዜሽን ስልጠናዎችን ጨምሮ የአካባቢውን ፀጋ ለመጠቀም የሚስችሉ ስልጠናዎች የሚሰጡ በመሆናቸው አውቅና እና ብቃት ወዳላቸው ኮሌጆች በማምራት የሥልጠና መስክ መምረጥ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በደረጃ 3 እና 4 ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ የመቀበል አዝማሚያዎች እንደነበሩ ያመላከቱት ኃላፊዋ በዚህ ዓመት ሁሉም የግል እና የመንግስት ኮሌጆች ደረጃ 1 እና 2 ተቀብለው ምዝገባ እንዲያካሂዱ አሳስበዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top