Mols.gov.et

የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ፍላጎት ልየታ…

January 18, 2024
የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ፍላጎት ልየታ፣ በሂደት ላይ ያሉ የሁለትዮሽ የሥራ ስምምነቶችን ማጠናቀቅ እና የተፈረሙትን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ማድረግ ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸው ተጠቆመ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዓመታዊ የአምባሳደሮች ስብሰባውን በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተገኝተው እየተከናወነ ባለው የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትና የክህሎት ልማት ስራዎች እንዲሁም ዘርፉን ለማዘመን የተዘረጋው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡ የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ፍላጎት ልየታ፣ በሂደት ላይ ያሉ የሁለትዮሽ የሥራ ስምምነቶችን ማጠናቀቅ እና የተፈረሙትን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ማድረግ ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች እንደሆኑ ክብርት ሚኒስትር በመድረኩ ላይ ገልፀዋል፡፡ ዘርፉ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የአቅም ማጎልበቻ መርሃ ግብሮችን በማመቻቸት ረገድ ከሚስዮንዎቹ ብዙ እንደሚጠበቅም ነው ክብርት ሚኒስትር የጠቆሙት፡፡
en_USEN
Scroll to Top