Mols.gov.et

የሰለጠነና በሙያቸው የበቁ ዜጎችን ከሥራ ጋር ለማስተሳሰር ከትላልቅ ኢንደስትሪዎች ጋር ተቀናጅቶ መስራት ፋይዳው የላቀ መሆኑ ተገለፀ፡፡

August 29, 2025
የሰለጠነና በሙያቸው የበቁ ዜጎችን ከሥራ ጋር ለማስተሳሰር ከትላልቅ ኢንደስትሪዎች ጋር ተቀናጅቶ መስራት ፋይዳው የላቀ መሆኑ ተገለፀ፡፡ የሲዳማ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና የዘረፉ ባለሙያዎች በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልል በአዳማ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የአዳማ ኢንዱሰትሪ ፓሪክ ANTEX ጋርመንት ካምፓኒ ጋር በመቀናጀት የሥራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች ያሉበት ሁኔታና የሥራ እንቅስቃሴያቸውን ጎበኙ። ቢሮው በክልሉ ውስጥ ያለው የስራ አጥነትን ችግር ለመቅረፍ እንደሀገር ያሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶችና ኢንደስትሪዎች ጋር በመቀናጀት በርካታ ወጣቶችን ከስራ ጋር ለማስተሳሰር በ2017 በጀት አመት የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተመቻቸላቸውን እድል በመጠቀም በስራ ላይ ያሉትን የስራ እንቅስቃሴና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም በ2018 በጀት አመትም ለሌሎች የሰለጠኑና ልምድ ያላቸው ዜጎች ተጨማሪ የስራ እድል በሚመቻችበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። በምክክሩ ላይ ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ለመፍጠር፣ በሠራተኛ ደህንነትና ጤንነት እንድሁም የተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር የጋራ ስምምነት እንደተፈጠረ ከሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
en_USEN
Scroll to Top