Mols.gov.et

የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ዘርፍን ለማሳደግ በባለድርሻ አካላት መካከል ጠንካራ ትብብር ሊኖር ይገባል ። ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚንስትር ድኤታ

October 19, 2023
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው በግብርና ምርት ማቀናበር ዘርፍ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል ። የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ባስተላለፉት መልዕክት የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ዘርፍ በርካታ ባለድርሻ አካላትን የሚያሳትፍ በመሆኑ በዘርፉ የሚጠበቀውን ውጤት ለማስመዝገብ በዘርፋ ተዋንያን መካከል ጠንካራ ትብብር ሊኖር ይገባል ብለዋል። የግብርና ምርት ማቀነባበር ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል ዘርፍ መሆኑን የገለፁት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ እና እሴት የታከለባቸው የግብርና ምርቶችን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚውን ከማሳደግ አንፃርም ጉልህ ድርሻ እንዳለው ጠቁመዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በዘርፉ ብቁ የሰው ሀይል ለማፍራት የሚያስችል የክህሎት የስልጠና ስርአዓትን አየዘረጋ እንደሚገኝ በመድረኩ የተጠቀሰ ሲሆን ስርዓተ ትምህርት የማዘጋጀትና ከኢንዱስትሪዎች ጋር በመተባበር ገበያ ተኮር ስልጠናዎችን የማመቻቸት ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝም ተብራርቷል ። የግብርና ምርትን ማቀነባበር ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም በመጠቀም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በዘርፉ የተሰማሩ አካላት በጋራ የሚሰሩበትን ምቹ ሁኔታ የማጠናከር ተግባርም በሚኒስቴር መ/ቤቱ እየተከናወነ ይገኛል ያሉት ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የጋራ እቅዶችን የሚያዘጋጅና ተግባራዊነታቸውን የሚከታተል የቴክኒክ ቡድን በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ እንደሚቋቋም ጠቁመዋል።
Scroll to Top