Mols.gov.et

የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት(LMIS) በሚሊኒየም አዳራሽ

October 18, 2023
የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት(LMIS) በሚሊኒየም አዳራሽ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከደረጃ ዶት ኮም እና ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር ባዘጋጁት ብሄራዊ የሥራ አውደ ርዕይ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ሥራ ፈላጊ የዩንቨርስቲ ምሩቃን የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት(LMIS) ምዝገባ ያለው ፋይዳ ላይ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጓል፡፡ ይህን ተከትሎ ተመራቂዎችም በተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸው የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓቱን እየተቀላቀሉ ይገኛል፡፡ በሀገሪቱ ስላሉ የሥራ ዕድሎች ጥልቅ መረጃ መስጠት ስለሚያስችለው የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት(LMIS) ፋይዳ እና የምዝገባ ሁኔታ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራም እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ የተመረጡ አንድ ማዕከላት የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት(LMIS) ምዝገባ እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል ፡፡
en_USEN
Scroll to Top