X
20%

Mols.gov.et

የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት(LMIS) ምዝገባ አዳማ

October 17, 2023
የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት(LMIS) ምዝገባ አዳማ ያለምንም እንግልት የምዝገባ አገልግሎት እያገኙ መሆኑን በአዳማ ከተማ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት(LMIS) ተመዝጋቢዎች ገለጹ፡፡ በአዳማ ከተማ በሚገኙ በመልካ አዳማ እና በድሬ ነጋ አንድ ማዕከላት ሲመዘገቡ ያገኘናቸው የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ተመዝጋቢዎች በየማዕከላቱ ቀልጣፋ አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በማዕከላቱ ተገኝተው ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ሲመዘገቡ ያገኘናቸው ከአርሲ አርባ ጉጉ ወረዳ የመጡት ወ/ሪት አሻ ፈቱኮ እና ከወለንጪቲ የመጡት ወ/ሪት ሲፋን ኬሎ እንደሚናገሩት የምዝገባ አገልግሎቱ ሳይቸገሩ እያገኙ ነው፡፡ በአዳማ ከተማ የድሬ ነጋ አንድ ማዕከል አስተባባሪ ያደታ ፍዳ እና የመልካ አዳማ አንድ ማዕክል አስተባባሪ ደረጄ ሮቢ በበኩላቸው ዜጎች ምዝገባውን በአግባቡ እና በተቀመጠለት አግባብ እንዲያገኙ ምሳ ሰዓትን ጨምሮ እስከ ምሽት ድረስ ገፍተው እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በሥራ ገበያ መረጃ ስርዓቱ ለመመዝገብ የሚፈልግ ማንኛውም ዜጋ በቅድሚያ በሚቀጥለው ማስፈንጠሪያ https://lmis.gov.et/ መመዝገብ ይኖርበታል። በምዝገባው ወቅት ስርዓቱ በሚሰጠው ሌበር አይዲ መሰረት በአቅራቢያው በሚገኝ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች በመገኘት የባዮ ሜትሪክስ ዳታ መስጠትና ምዝገባውን ማጠናቀቅ ይችላሉ፡፡
en_US