Mols.gov.et

የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ በተመረጡ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ተግባራዊ መሆን ጀመረ

August 26, 2023
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በልጽጎ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት የሰራተኛና የሥራ መረጃዎችን በዘመናዊ መንገድ በማስተዳደር ዜጎች በሃገር ውስጥና በውጭ ሀገር በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ስርዓት ነው። በመጀመሪያ ምዕራፍ ሥርዓቱን በአዲስ አበባ ዋናው መስሪያ ቤት ብቻ ተግባራዊ እየተደረገ ቆይቷል፡፡ በቅርቡ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች በሚገኙ የተመረጡ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ሥርዓቱን ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ በዚህም ለተግባራዊነቱ የሚያስፍልጉ የባዮሜትሪክስ፣ የላፕቶፕ፣ የዋይፋይ ራውተር እና ሌሎች ቁሳቁሶች l000 ለሚሆኑ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ለማሟላት ታቅዶ የተመረጡና 400 ለሚሆኑት ስርጭት እየተከናወነ ይገኛል። በመሆኑም የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓቱ በኦሮሚያ ክልል በአምቦ፣ በሻሸመኔ፣ በአዳማ፣ በአሰላ፣ በቡራዩ፣ በምስራቅ ሃረርጌ፣ በመትሃራ፣ በፉሪ፣ በጉደር እና በጅማ፤ በአዲስ አበባ በቦሌ፣ በየካ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በአዲ ከተማ እና በኮልፌ ክፍለ ከተሞች፤ በሲዳማ ክልል በሃዋሳ፣ ባንሳ፣ አለታ ወንዶ እና በወንዶ ገነት እንዲሁም በደበብ ምዕራብ በቴፒና ሌሎች ከተማ በሚገኙ የተወሰኑ አንድ ማዕከላት አገልግሎት መስጠት ተጀምሯል። በዚህም ከዚህ ቀደም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ ለማድረግ ባስተላለፈው የምዝገባ ጥሪ መሰረት ከ180,000 በላይ ዜጎች በድረ-ገጽ (በኦን ላይን) ተመዝግበው የባዮሜትሪክስ ምዝገባ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም ከላይ በተጠቀሱትና በሚቀርባቸው የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ተገኝተው አስፈልጊውን አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ ሲሆን መረጃ ሞልተው የባዮሜትሪክስ ምዝገባን በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ስርጭትና ምዝገባ ያልደረሰባቸው የአንድ ማዕከላት ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አነሁንም የስርዓቱ ተጠቃሚ ለመሆን ፍላጎት ያለው ማንኛውም ሰው ከዚህ በታች በሚገኘው ማስፈንጠሪያ (https://www.lmis.gov.et) አስፈላጊውን መረጃ በመሙላት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በድጋሚ እናሳውቃለን፡፡
en_USEN
Scroll to Top