Mols.gov.et

Project

የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እና ሌሎች የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተጠሪ ተቋማት በደቡብ ወሎ ዞን በአሸባሪው ህወሀት ወረራ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ::

Nov 16 , 2021 

የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ተወካዮች ከሌሎች የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን አሸባሪው ህውሀት በከፈተው ጥቃት ምክንያት ከአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተጠልለው ለሚገኙ ወገኖች የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን የተቀናጀ የመረጃ ትንተና እና ሥርዓት ማበልፀጊያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ሠርፀ የተደረገው ድጋፍ የተፈናቀሉ ወገኖችን ” አይዟችሁ! አለንላችሁ! ለማለት ነው” ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የኮሚሽኑ እና ሌሎች የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ዘመቻ የአቅመ ደካሞችን ቤት እድሳት መርሐግብርን በቃሉ ወረዳ ገርባ እና ደጋን ቀበሌ እንዲሁም በሀርቡ ከተማ አስተዳደር አስጀምረዋል፡፡
Scroll to Top