Mols.gov.et

የሥራ ዕድል ፈጠራ ለሰላም ግንባታ …

January 23, 2024
የሥራ ዕድል ፈጠራ ለሰላም ግንባታ … የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነትን ተከትሎ የፌዴራል ተቋማት በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያሉ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም በሙሉ አቅማቸው እንዲደግፉ በተቀመጠው የመንግስትና የፓርቲ አቅጣጫ መሰረት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የበኩሉን ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም 2000 ወጣቶችን ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችል የሥልጠናና የፋይናንስ ድጋፍ እና 3000 ኢንተርፕራይዞችን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል ፕሮግራም ይፋ ሲሆን የ65 ሚሊዮን ግምት ያለው ቁሳቁስ ከክልሎች፣ ከተጠሪ ተቋማት እና ከሚንስቴር መስሪያቤቱ የተገኘ እገዛ ድጋፍ ተደርጓል። ለተደረገው ድጋፍ የልማት አጋራችን የሆነው የማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ ፈርስት ኮንሰልት እና የአለም ባንክ እንዲሁም ለነበረን ቆይታ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ጌታቸው ረዳና ባልደረቦቻቸው ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡
en_USEN
Scroll to Top