Mols.gov.et

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አዲሱ እሳቤ ከማሰልጠንና ዳቦ በልቶ ከማደር ያለፈ ጥራት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር፣ አዲስ የኢንዱስትሪ ባህል በመገንባት ምርታማነትን መጨመር እና ችግሮችን ወደ መልካም ዕድል መቀየር ነው

August 22, 2022
ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ዘላቂ ጉዞን በአዲስ አስተሳሰብ መቃኘትን መሰረት ያደረገ ስልጠና ጀምረዋል። በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የሀገረ መንግስት እና የሀገረ ብሔር ግንባታ ችግሮችን አበይት ተግዳሮቶች መሆናቸውን ተናግረዋል። የሀገረ መንግስት ግንባታ በዋናነት ነፃና ገለልተኛ ተቋማት መገንባትን መሰረት የሚያደርግ ሲሆን ተቋማትን የስርዓት ሳይሆን የዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ የለውጡ መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል። ሀገርና ህዝብ ዘመን ተሻጋሪ በመሆናቸው የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳላቸውም ገልፀዋል። ሀገር እና ህዝብን ማዕከል በማድረግ በተሰሩ ሥራዎች ሩቅ የነበሩ ተቋማትን ማቅረብ መቻሉን የተናገሩት ክብርት ሚኒስትር ሙፈሪሃት የሰው ኃይልን ዝግጁ አድርጎ ሀገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ምን አይነት መዋቅራዊ ችግርን መፍታት ይጠበቃል ለሚለው መልስ መስጠት አስፈላጊ ነው ብለዋል። ሀገር ወዳድ እና ዝግጁ ትውልድ መገንባትም ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ሲገልፁ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አዲሱ እሳቤዎች የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከማሰልጠንና ዳቦ በልቶ ከማደር ያለፈ ጥራት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር፣ አዲስ የኢንዱስትሪ ባህል በመገንባት ምርታማነትን መጨመር እና ችግሮችን ወደ መልካም ዕድል መቀየር ነው ብለዋል ።
en_USEN
Scroll to Top