Mols.gov.et

የሥራ ባህልን በማሳደግ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ምርትና ምርታማነትን ለማሣደግ በትኩረት እየተሠራ ነው። ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

November 6, 2024
የሥራ ባህልን በማሳደግ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ምርትና ምርታማነትን ለማሣደግ በትኩረት እየተሠራ ነው። ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ 5ኛው ሀገር አቀፍ ብሔራዊ የሥራ ኤክስፖ በአዲስ አበባ የሚሊኒየም አዳራሽ ተክፍቷል ፡፡ ኤክስፓው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከደረጃ ዶት ኮም እና ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው። በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት፣ መንግሥት ለዜጎች ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር በትኩረት እየሠራ ይገኛል ብለዋል። ከደረጃ ዶት ኮም እና ከማስተርካርድ ፋውንዴሽ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ የሥራ ኤክስፖ ሥራ ፈላጊዎች እና ቀጣሪ ድርጅቶችን ለማገናኘትና የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያለመ ነው። ይህም ከ30ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ያስችላል ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ኤክስፓው ለሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑን አመላክተዋል። የሥራ ባህልን በማሳደግ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ምርትና ምርታማነትን ለማሣደግ እንዲሁም ቤተሰብንና ማህበረሰብን የምርታማነት ማዕከል ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። በመድረኩ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶክተር ተሻለ በሬቻን፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሙና አህመድ፣ የትምህት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ አቶ ሳሙኤል ያለው የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ካንትሪ ዳይሬክተር፣ አቶ የሱፍ ረጃ የኢትዮ ጆብስ እና ደረጃ እናት ኩባንያ የሆነው የአፍሪካ ጆብስ ኔትወርክ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተገኝተዋል።
en_USEN
Scroll to Top