“የሥራ ላይ ልምምድ ለወጣቶች ዘላቂ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ የላቀ ድርሻ አለው”
ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
‹‹ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም›› ሁለተኛ ዙር ትግበራ በሐዋሳ ከተማ በይፋ ተጀምሯል፡፡
በፕሮግራሙ ማብሰሪያ መድረክ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ የሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ለወጣቶች የተሟላ ክህሎት በማላበስ ዘላቂ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ድርሻው የላቀ ነው ብለዋል፡፡
የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች ወደ ሥራ ላይ ልምምድ ከመሰማራታቸው በፊት የህይወት ክህሎት፣ የሥራ ፈጠራ፣ የኮምፒውተርና ሙያዊ ክህሎት ሥልጠናዎችን በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አማካኝነት ማግኘታቸው ለሥራ ገበያው ራሳቸውን ለማዘጋጀት እንዳስቻለቸው ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስረድተዋል፡፡
ወጣቶቹ በዚህ መልኩ ያደረጉት ቅድመ ዝግጀት በተሠማሩበት የሥራ ላይ ልምምድ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር ጉልህ አበርክቶ ነበረው በማለት የሚገልፁት ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን በዚህም መሠረት በሐዋሳ ከተማ በ110 ድርጅቶች ውስጥ ለስድስት ወራት የሥራ ላይ ልምምድ ሲያደርጉ የቆዩ 868 ወጣቶችን ወደ ቅጥር የሥራ መስክ ላይ መሰማራታቸውን አብራርተዋል፡፡