Mols.gov.et

NEWS

የሥራና ክህሎት ፣ የግብርና እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ለሥራ ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት እና የሥራ ዕድል መፍጠርን በተመለከተ ተወያዩ።

Nov 17, 2021 

የሥራና ክህሎት ፣ የግብርና እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ለሥራ ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት እና የሥራ ዕድል መፍጠርን በተመለከተ ተወያዩ።
ሚኒስትሮቹ ዘርፎቹን ውጤታማ ለማድረግ ብቃት ያለውና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለማፍራትና በመስኩ ሊፈጠር የሚገባውን የሥራ ዕድል በስፋትና በብቃት ለመፍጠር ሊከናወኑ የሚገባቸው ተግባራት እንዲሁም በቀጣይ የቅንጅትና ትብብር ተቋማዊ አሰራሮች የሚዘረጉበት ሁኔታ ላይ ምክክር አድርገው ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል::
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ኢኮኖሚው የተረጋጋና ተወዳዳሪ ሆኖ ሊቀጥል ከሆነ በጠንካራ ቅንጅታዊ ትስስር በየመስኩ ያሉ እምቅ አቅሞችን ማውጣት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
የሁለቱም ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች በርካታ ገንቢ ሀሳቦችን በመሰንዘር ለተግባራዊነቱ ያላቸውን ቁርጠኝነት ተናግረው አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ በመግለፅ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለወሰደው ተነሳሽነት አክብሮታቸውን ችረዋል።
ይህ ቅንጅትና ትብብር ከሌሎች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ተቋማት ጋርም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል::
en_USEN
Scroll to Top